መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #65
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 65 |
Psalm 65 |
1 አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ጸሎት ይቀርባል። |
1 Praise waiteth for thee, O God, in Sion: and unto thee shall the vow be performed. |
2 ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል። |
2 O thou that hearest prayer, unto thee shall all flesh come. |
3 የዓመፃ ነገር በረታብን ኃጢአታችንንስ አንተ ይቅር ትላለህ። |
3 Iniquities prevail against me: as for our transgressions, thou shalt purge them away. |
4 አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው ከቤትህ በረከት እንጠግባለን። |
4 Blessed is the man whom thou choosest, and causest to approach unto thee, that he may dwell in thy courts: we shall be satisfied with the goodness of thy house, even of thy holy temple. |
5 ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ ስማን። |
5 By terrible things in righteousness wilt thou answer us, O God of our salvation; who art the confidence of all the ends of the earth, and of them that are afar off upon the sea: |
6 በጉልበትህ ተራሮችን አጸናሃቸው፥ በኃይልም ታጥቀሃል። |
6 Which by his strength setteth fast the mountains; being girded with power: |
7 የባሕሩን ጥልቀት የሞገድንም ጩኸት ታናውጣለህ። |
7 Which stilleth the noise of the seas, the noise of their waves, and the tumult of the people. |
8 ከተአምራትህ የተነሣ አሕዛብ ይደነግጣሉ፥ በምድር ዳርቻም የሚኖሩ ይፈራሉ የጥዋትንና የማታን መውጫ ደስ ታሰኛቸዋለህ። |
8 They also that dwell in the uttermost parts are afraid at thy tokens: thou makest the outgoings of the morning and evening to rejoice. |
9 ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም፥ ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ የእግዚአብሔርን ወንዝ ውኃን የተመላ ነው ምግባቸውን አዘጋጀህ እንዲሁ ታሰናዳለህና። |
9 Thou visitest the earth, and waterest it: thou greatly enrichest it with the river of God, which is full of water: thou preparest them corn, when thou hast so provided for it. |
10 ትልምዋን ታረካለህ፥ ቦይዋንም ታስተካክላለህ በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ፥ ቡቃያዋንም ትባርካለህ። |
10 Thou waterest the ridges thereof abundantly: thou settlest the furrows thereof: thou makest it soft with showers: thou blessest the springing thereof. |
11 በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። |
11 Thou crownest the year with thy goodness; and thy paths drop fatness. |
12 የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። |
12 They drop upon the pastures of the wilderness: and the little hills rejoice on every side. |
13 ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም። |
13 The pastures are clothed with flocks; the valleys also are covered over with corn; they shout for joy, they also sing. |