ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #26
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 26

Genesis 26

1 በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ በላይ ራብ ሆነ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቢሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።

1 And there was a famine in the land, beside the first famine that was in the days of Abraham. And Isaac went unto Abimelech king of the Philistines unto Gerar.

2 እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ ወደ ግብፅ አትውረድ፥ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ።

2 And the Lord appeared unto him, and said, Go not down into Egypt; dwell in the land which I shall tell thee of:

3 በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።

3 Sojourn in this land, and I will be with thee, and will bless thee; for unto thee, and unto thy seed, I will give all these countries, and I will perform the oath which I sware unto Abraham thy father;

4 ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ የምድርም አህዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ

4 And I will make thy seed to multiply as the stars of heaven, and will give unto thy seed all these countries; and in thy seed shall all the nations of the earth be blessed;

5 አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።

5 Because that Abraham obeyed my voice, and kept my charge, my commandments, my statutes, and my laws.

6 ይስሐቅም በጌራራ ተቀመጠ።

6 And Isaac dwelt in Gerar:

7 የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት እርሱም፦ እኅቴ ናት አለ የዚህ ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና እርስዋ ውብ ነበረችና።

7 And the men of the place asked him of his wife; and he said, She is my sister: for he feared to say, She is my wife; lest, said he, the men of the place should kill me for Rebekah; because she was fair to look upon.

8 በዚያም ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ሆኖ ጎበኘ፥ ይስሐቅም ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ።

8 And it came to pass, when he had been there a long time, that Abimelech king of the Philistines looked out at a window, and saw, and, behold, Isaac was sporting with Rebekah his wife.

9 አቢሜሌክም ይስሐቅን ጠራ፥ እንዲህም አለው፦ እነሆ ሚስትህ ናት እንዴትስ እርስዋን፦ እኅቴ ናት አልህ? ይስሐቅም፦ በእርስዋ ምክንያት እንዳልሞት ብዬ ነው አለው።

9 And Abimelech called Isaac, and said, Behold, of a surety she is thy wife: and how saidst thou, She is my sister? And Isaac said unto him, Because I said, Lest I die for her.

10 አቢሜሌክም አለ፦ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ከሕዝብ አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀረው ነበር፥ ኃጢአትንም ልታመጣብን ነበር።

10 And Abimelech said, What is this thou hast done unto us? one of the people might lightly have lien with thy wife, and thou shouldest have brought guiltiness upon us.

11 አቢሜሌክም ሕዝቡን ሁሉ፦ ይህን ሰው ሚስቱንም የሚነካ ሞትን ይሙት ብሎ አዘዘ።

11 And Abimelech charged all his people, saying, He that toucheth this man or his wife shall surely be put to death.

12 ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ እግዚአብሔርም ባረከው።

12 Then Isaac sowed in that land, and received in the same year an hundredfold: and the Lord blessed him.

13 ባለ ጠጋ ሰውም ሆነ፥ እጅግ እስኪበልጥ ድረስም እየጨመረ ይበዛ ነበር

13 And the man waxed great, and went forward, and grew until he became very great:

14 የበግና የላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት።

14 For he had possession of flocks, and possession of herds, and great store of servants: and the Philistines envied him.

15 በአባቱ በአብርሃም ዘመን የአባቱ ሎሌዎች የማሱአቸውን ጕድጓዶች ሁሉ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑአቸው አፈርንም ሞሉባቸው።

15 For all the wells which his father’s servants had digged in the days of Abraham his father, the Philistines had stopped them, and filled them with earth.

16 አቢሜሌክም ይስሐቅን፦ ከእኛ ተለይተህ ሂድ፥ ከእኛ ይልቅ እጅግ በርትተሃልና አለው።

16 And Abimelech said unto Isaac, Go from us; for thou art much mightier than we.

17 ይስሐቅም ከዚያ ሄደ፥ በጌራራም ሸለቆ ሰፍሮ በዚያ ተቀመጠ።

17 And Isaac departed thence, and pitched his tent in the valley of Gerar, and dwelt there.

18 ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ዘመን ቈፍረዋቸው የነበሩትን የውኃ ጕድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ አብርሃም ከሞተ በኋላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበሩና አባቱም ይጠራቸው በነበረው ስም ጠራቸው።

18 And Isaac digged again the wells of water, which they had digged in the days of Abraham his father; for the Philistines had stopped them after the death of Abraham: and he called their names after the names by which his father had called them.

19 የይስሐቅ ሎሌዎችም በሸለቆው ውስጥ ቈፈሩ፥ በዚያም የሚመነጭ የውኃ ጕድጓድ አገኙ።

19 And Isaac’s servants digged in the valley, and found there a well of springing water.

20 የጌራራ አገር እረኞች ከይስሐቅ እረኞች ጋር፦ ውኃው የእኛ ነው ሲሉ ተከራከሩ የዚያችንም ጕድጓድ ስም ኤሴቅ ብሎ ጠራት፥ ለእርስዋ ሲሉ ተጣልተዋልና።

20 And the herdmen of Gerar did strive with Isaac’s herdmen, saying, The water is ours: and he called the name of the well Esek; because they strove with him.

21 ሌላ ጕድጓድም ማሱ፥ ስለ እርስዋም ደግሞ ተጣሉ ስምዋንም ስጥና ብሎ ጠራት።

21 And they digged another well, and strove for that also: and he called the name of it Sitnah.

22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ አስቈፈረ፥ ስለ እርስዋም አልተጣሉም ስምዋንም ርኆቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።

22 And he removed from thence, and digged another well; and for that they strove not: and he called the name of it Rehoboth; and he said, For now the Lord hath made room for us, and we shall be fruitful in the land.

23-24 ከዚያም ወደ ቤርሳቤህ ወጣ። በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና እባርክሃለሁ ስለ ባሪያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።

23 And he went up from thence to Beer–sheba.
24 And the Lord appeared unto him the same night, and said, I am the God of Abraham thy father: fear not, for I am with thee, and will bless thee, and multiply thy seed for my servant Abraham’s sake.

25 በዚያም መሠዊያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፥ በዚያም ድንኳን ተከለ የይስሐቅም ሎሌዎች በዚያ ጕድጓድ ማሱ።

25 And he builded an altar there, and called upon the name of the Lord, and pitched his tent there: and there Isaac’s servants digged a well.

26 አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱም አለቃ ፊኮል ከጌራራ ወደ እርሱ ሄዱ።

26 Then Abimelech went to him from Gerar, and Ahuzzath one of his friends, and Phichol the chief captain of his army.

27 ይስሐቅም፦ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል፥ ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛል አላቸው።

27 And Isaac said unto them, Wherefore come ye to me, seeing ye hate me, and have sent me away from you?

28-29 እነርሱም አሉት፦ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ በእርግጥ አየን ስለዚህም፦ በእኛና በአንተ መካከል መሐላ ይሁን እኛ አንተን እንዳልነካንህ፥ በጎነትንም ብቻ እንዳሳየንህ፥ በደኅናም እንደ ሰደድንህ፥ አንተም ክፉ እንዳትሠራብን ቃል ኪዳን ከአንተ ጋር እናድርግ አልን አንተ አሁን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረክህ ነህ።

28 And they said, We saw certainly that the Lord was with thee: and we said, Let there be now an oath betwixt us, even betwixt us and thee, and let us make a covenant with thee;
29 That thou wilt do us no hurt, as we have not touched thee, and as we have done unto thee nothing but good, and have sent thee away in peace: thou art now the blessed of the Lord.

30 ይስሐቅም ማዕድ አቀረበላቸው፥ በሉም ጠጡም።

30 And he made them a feast, and they did eat and drink.

31 ማልደውም ተነሡ፥ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ ይስሐቅም አሰናበታቸው፥ ከእርሱም ወጥተው በደኅና ሄዱ።

31 And they rose up betimes in the morning, and sware one to another: and Isaac sent them away, and they departed from him in peace.

32 በዚያም ቀን የይስሐቅ ሎሌዎች መጡ፥ ስለቈፈሩአትም ጕድጓድ፦ ውኃ አገኘን ብለው ነገሩት።

32 And it came to pass the same day, that Isaac’s servants came, and told him concerning the well which they had digged, and said unto him, We have found water.

33 ስምዋንም ሳቤህ ብሎ ጠራት ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ነው።

33 And he called it Shebah: therefore the name of the city is Beer–sheba unto this day.

34 ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ

34 And Esau was forty years old when he took to wife Judith the daughter of Beeri the Hittite, and Bashemath the daughter of Elon the Hittite:

35 እነርሱም የይስሐቅንና የርብቃን ልብ ያሳዝኑ ነበር።

35 Which were a grief of mind unto Isaac and to Rebekah.