ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #29
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 29

Exodus 29

1 እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግባቸው ነገር ይህ ነው ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ትወስዳለህ።

1 And this is the thing that thou shalt do unto them to hallow them, to minister unto me in the priest’s office: Take one young bullock, and two rams without blemish,

2 ቂጣ እንጀራ፥ በዘይትም የተለወሰ የቂጣ እንጐቻ፥ በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ ከመልካም ስንዴ ታደርጋለህ።

2 And unleavened bread, and cakes unleavened tempered with oil, and wafers unleavened anointed with oil: of wheaten flour shalt thou make them.

3 በአንድ ሌማትም ታደርጋቸዋለህ ከወይፈኑና ከሁለቱ አውራ በጎች ጋር በሌማቱ ታቀርባቸዋለህ።

3 And thou shalt put them into one basket, and bring them in the basket, with the bullock and the two rams.

4 አሮንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ታቀርባቸዋለህ፥ በውኃም ታጥባቸዋለህ።

4 And Aaron and his sons thou shalt bring unto the door of the tabernacle of the congregation, and shalt wash them with water.

5 ልብሶችን ወስደህ ለአሮን ሸሚዝና የኤፉድ ቀሚስ ኤፉድም የደረት ኪስም ታለብሰዋለህ፥ በብልሃትም በተጠለፈ ቋድ ታስታጥቀዋለህ

5 And thou shalt take the garments, and put upon Aaron the coat, and the robe of the ephod, and the ephod, and the breastplate, and gird him with the curious girdle of the ephod:

6 መጠምጠሚያውንም በራሱ ላይ ታደርጋለህ፥ የተቀደሰውንም አክሊል በመጠምጠሚያው ላይ ታኖራለህ።

6 And thou shalt put the mitre upon his head, and put the holy crown upon the mitre.

7 የቅብዓትንም ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈስሰዋለህ፥ ትቀባውማለህ።

7 Then shalt thou take the anointing oil, and pour it upon his head, and anoint him.

8 ልጆቹንም ታቀርባቸዋለህ፥ ሸሚዞቹንም ታለብሳቸዋለህ።

8 And thou shalt bring his sons, and put coats upon them.

9 አሮንንና ልጆቹንም በመታጠቂያ ታስታጥቃቸዋለህ፥ ቆብንም ታለብሳቸዋለህ ለዘላለም ሥርዓትም ክህነት ይሆንላቸዋል እንዲሁም አሮንንና ልጆቹን ትክናቸዋለህ።

9 And thou shalt gird them with girdles, Aaron and his sons, and put the bonnets on them: and the priest’s office shall be theirs for a perpetual statute: and thou shalt consecrate Aaron and his sons.

10 ወይፈኑንም ወደ መገናኛው ድንኳን በር ፊት ታቀርበዋለህ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናሉ።

10 And thou shalt cause a bullock to be brought before the tabernacle of the congregation: and Aaron and his sons shall put their hands upon the head of the bullock.

11 ወይፈኑንም በመገናኛው ድንኳን በር አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ታርደዋለህ።

11 And thou shalt kill the bullock before the Lord, by the door of the tabernacle of the congregation.

12 ከወይፈኑም ደም ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ በጣትህ ትረጨዋለህ ደሙንም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ታፈስሰዋለህ።

12 And thou shalt take of the blood of the bullock, and put it upon the horns of the altar with thy finger, and pour all the blood beside the bottom of the altar.

13 የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ በጉልበቱም ላይ ያለውን መረብ ሁለቱንም ኵላሊቶች በላያቸውም ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ።

13 And thou shalt take all the fat that covereth the inwards, and the caul that is above the liver, and the two kidneys, and the fat that is upon them, and burn them upon the altar.

14 የወይፈኑን ሥጋ ግን፥ ቁርበቱንም፥ ፈርሱንም ከሰፈር ውጭ በእሳት ታቃጥለዋለህ የኃጢአት መሥዋዕት ነው።

14 But the flesh of the bullock, and his skin, and his dung, shalt thou burn with fire without the camp: it is a sin offering.

15 አንደኛውንም አውራ በግ ትወስደዋለህ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጭናሉ።

15 Thou shalt also take one ram; and Aaron and his sons shall put their hands upon the head of the ram.

16 አውራውንም በግ ታርደዋለህ፥ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ትረጨዋለህ።

16 And thou shalt slay the ram, and thou shalt take his blood, and sprinkle it round about upon the altar.

17 አውራውንም በግ በየብልቱ ትቈርጠዋለህ፥ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም ታጥባለህ፥ ከብልቱና ከራሱም ጋር ታኖረዋለህ።

17 And thou shalt cut the ram in pieces, and wash the inwards of him, and his legs, and put them unto his pieces, and unto his head.

18 አውራውንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው ጣፋጭ ሽቱ ነው። ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው።

18 And thou shalt burn the whole ram upon the altar: it is a burnt offering unto the Lord: it is a sweet savour, an offering made by fire unto the Lord.

19 ሁለተኛውንም አውራ በግ ትወስደዋለህ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ይጭናሉ።

19 And thou shalt take the other ram; and Aaron and his sons shall put their hands upon the head of the ram.

20 አውራውንም በግ ታርደዋለህ፥ ደሙንም ትወስዳለህ፥ የአሮንንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የልጆቹንም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ታስነካለህ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ትረጨዋለህ።

20 Then shalt thou kill the ram, and take of his blood, and put it upon the tip of the right ear of Aaron, and upon the tip of the right ear of his sons, and upon the thumb of their right hand, and upon the great toe of their right foot, and sprinkle the blood upon the altar round about.

21 በመሠዊያውም ላይ ካለው ደም ከቅብዓት ዘይትም ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ ከእርሱም ጋር ባሉት በልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ ትረጨዋለህ እርሱም ልብሶቹም፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹ ልብሶቻቸውም ይቀደሳሉ።

21 And thou shalt take of the blood that is upon the altar, and of the anointing oil, and sprinkle it upon Aaron, and upon his garments, and upon his sons, and upon the garments of his sons with him: and he shall be hallowed, and his garments, and his sons, and his sons’ garments with him.

22 ደግሞም የሚካኑበት አውራ በግ ነውና የበጉን ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች በላያቸውም ያለውን ስብ፥ የቀኙንም ወርች ትወስዳለህ።

22 Also thou shalt take of the ram the fat and the rump, and the fat that covereth the inwards, and the caul above the liver, and the two kidneys, and the fat that is upon them, and the right shoulder; for it is a ram of consecration:

23 አንድ እንጀራ፥ አንድም የዘይት እንጀራ፥ አንድም ስስ ቂጣ በእግዚአብሔር ፊት በሌማት ካለው ቂጣ እንጀራ ትወስዳለህ

23 And one loaf of bread, and one cake of oiled bread, and one wafer out of the basket of the unleavened bread that is before the Lord:

24 ሁሉንም በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታኖረዋለህ ለሚወዘወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትወዘውዘዋለህ።

24 And thou shalt put all in the hands of Aaron, and in the hands of his sons; and shalt wave them for a wave offering before the Lord.

25 ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፥ በመሠዊያውም ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በእግዚአብሔር ፊት ጣፋጭ ሽቱ እንዲሆን ታቃጥለዋለህ እርሱ ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነው።

25 And thou shalt receive them of their hands, and burn them upon the altar for a burnt offering, for a sweet savour before the Lord: it is an offering made by fire unto the Lord.

26 ለአሮንም ክህነት የታረደውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚወዘወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትወዘውዘዋለህ እርሱም የአንተ ወግ ይሆናል።

26 And thou shalt take the breast of the ram of Aaron’s consecration, and wave it for a wave offering before the Lord: and it shall be thy part.

27 ከሚካኑበትም አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ወግ የሚሆን ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።

27 And thou shalt sanctify the breast of the wave offering, and the shoulder of the heave offering, which is waved, and which is heaved up, of the ram of the consecration, even of that which is for Aaron, and of that which is for his sons:

28 ያውም የማንሣት ቍርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ለዘላለም የአሮንና የልጆቹ ወግ ይሁን የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የደኅንነት መሥዋዕታቸው የማንሣት ቍርባን ይሆናል ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን ይሆናል።

28 And it shall be Aaron’s and his sons’ by a statute for ever from the children of Israel: for it is an heave offering: and it shall be an heave offering from the children of Israel of the sacrifice of their peace offerings, even their heave offering unto the Lord.

29 የተቀደሰውም የአሮን ልብስ ይቀቡበትና ይካኑበት ዘንድ ከእርሱ በኋላ ለልጆቹ ይሁን።

29 And the holy garments of Aaron shall be his sons’ after him, to be anointed therein, and to be consecrated in them.

30 ከልጆቹም በእርሱ ፋንታ ካህን የሚሆነው በመቅደስ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይልበሰው።

30 And that son that is priest in his stead shall put them on seven days, when he cometh into the tabernacle of the congregation to minister in the holy place.

31 የሚካንበትንም አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ።

31 And thou shalt take the ram of the consecration, and seethe his flesh in the holy place.

32 አሮንና ልጆቹም የአውራውን በግ ሥጋ በሌማትም ያለውን እንጀራ በመገናኛው ድንኳን በር ይበሉታል።

32 And Aaron and his sons shall eat the flesh of the ram, and the bread that is in the basket, by the door of the tabernacle of the congregation.

33 የተካኑና የተቀደሱ ይሆኑ ዘንድ ማስተስረያ የሆነውን ነገር ይብሉት ሌላ ሰው ግን አይብላው የተቀደሰ ነውና።

33 And they shall eat those things wherewith the atonement was made, to consecrate and to sanctify them: but a stranger shall not eat thereof, because they are holy.

34 የተካኑበትም ሥጋ ወይም እንጀራ ተርፎ ቢያድር፥ የቀረውን በእሳት ታቃጥለዋለህ የተቀደሰ ነውና አይበላም።

34 And if ought of the flesh of the consecrations, or of the bread, remain unto the morning, then thou shalt burn the remainder with fire: it shall not be eaten, because it is holy.

35 እንዳዘዝሁህም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ እንዲህ አድርግ ሰባት ቀን ትክናቸዋለህ።

35 And thus shalt thou do unto Aaron, and to his sons, according to all things which I have commanded thee: seven days shalt thou consecrate them.

36 ዕለት ዕለትም ስለ ማስተስረይ ለኃጢአት መሥዋዕት ወይፈኑን ታቀርባለህ ማስተስረያም ባደረግህ ጊዜ መሠዊያውን ታነጻዋለህ ቅዱስም ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ።

36 And thou shalt offer every day a bullock for a sin offering for atonement: and thou shalt cleanse the altar, when thou hast made an atonement for it, and thou shalt anoint it, to sanctify it.

37 ሰባት ቀን ለመሠዊያው ማስተስረያ ታደርጋለህ፥ ትቀድሰውማለህ መሠዊያውም ቅድስተ ቅዱሳን ይሆናል መሠዊያውንም የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።

37 Seven days thou shalt make an atonement for the altar, and sanctify it; and it shall be an altar most holy: whatsoever toucheth the altar shall be holy.

38 በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው ይህ ነው በቀን በቀን ዘወትር ሁለት የዓመት ጠቦቶች ታቀርባለህ።

38 Now this is that which thou shalt offer upon the altar; two lambs of the first year day by day continually.

39 አንዱን ጠቦት በማለዳ ቍርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ ሁለተኛውንም ጠቦት በማታ ቍርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ።

39 The one lamb thou shalt offer in the morning; and the other lamb thou shalt offer at even:

40 ከአንዱ ጠቦትም ጋር የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመጠጥ ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ።

40 And with the one lamb a tenth deal of flour mingled with the fourth part of an hin of beaten oil; and the fourth part of an hin of wine for a drink offering.

41 ሁለተኛውንም ጠቦት በማታ ታቀርበዋለህ፥ እንደ ማለዳውም የእህልና የመጠጥ ቍርባን ታደርግበታለህ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽቱ እንዲሆን የእሳት ቍርባን ይሆናል።

41 And the other lamb thou shalt offer at even, and shalt do thereto according to the meat offering of the morning, and according to the drink offering thereof, for a sweet savour, an offering made by fire unto the Lord.

42 ለአንተ እናገር ዘንድ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ፥ በእግዚአብሔር ፊት ይህ ዘወትር ለልጅ ልጃችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል።

42 This shall be a continual burnt offering throughout your generations at the door of the tabernacle of the congregation before the Lord: where I will meet you, to speak there unto thee.

43 ከእስራኤልም ልጆች ጋር በዚያ እገናኛለሁ ድንኳኑም በክብሬ ይቀደሳል።

43 And there I will meet with the children of Israel, and the tabernacle shall be sanctified by my glory.

44 የመገናኛውንም ድንኳን መሠዊያውንም እቀድሳለሁ በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን እቀድሳለሁ።

44 And I will sanctify the tabernacle of the congregation, and the altar: I will sanctify also both Aaron and his sons, to minister to me in the priest’s office.

45 በእስራኤልም ልጆች መካከል እኖራለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።

45 And I will dwell among the children of Israel, and will be their God.

46 በመካከላቸውም እኖር ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አምላካቸው እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝ።

46 And they shall know that I am the Lord their God, that brought them forth out of the land of Egypt, that I may dwell among them: I am the Lord their God.