መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #92
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 92 |
Psalm 92 |
1 እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ |
1 It is a good thing to give thanks unto the Lord, and to sing praises unto thy name, O most High: |
2 በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት |
2 To shew forth thy lovingkindness in the morning, and thy faithfulness every night, |
3 አሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ። |
3 Upon an instrument of ten strings, and upon the psaltery; upon the harp with a solemn sound. |
4 አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና። |
4 For thou, Lord, hast made me glad through thy work: I will triumph in the works of thy hands. |
5 አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ትልቅ ነው፥ አሳብህም እጅግ ጥልቅ ነው። |
5 O Lord, how great are thy works! and thy thoughts are very deep. |
6 ሰነፍ ሰው አያውቅም። ልብ የሌለውም ይህን አያስተውለውም። |
6 A brutish man knoweth not; neither doth a fool understand this. |
7 ኃጢአተኞች እንደ ሣር ሲበቅሉ ዓመፃ የሚያደርጉ ሁሉ ሲለመልሙ፥ ለዘላለም ዓለም እንዲጠፋ ነው። |
7 When the wicked spring as the grass, and when all the workers of iniquity do flourish; it is that they shall be destroyed for ever: |
8 አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘላለም ልዑል ነህ |
8 But thou, Lord, art most high for evermore. |
9 አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፥ ዓመፃንም የሚሠሩ ሁሉ ይበተናሉና። |
9 For, lo, thine enemies, O Lord, for, lo, thine enemies shall perish; all the workers of iniquity shall be scattered. |
10 ቀንዴ አንድ ቀንድ እንዳለው ከፍ ከፍ ይላል ሽምግልናዬም በዘይት ይለመልማል። |
10 But my horn shalt thou exalt like the horn of an unicorn: I shall be anointed with fresh oil. |
11 ዓይኔም በጠላቶቼ ላይ አየች፥ ጆሮዬም በእኔ ላይ በቆሙ በክፉዎች ላይ ሰማች። |
11 Mine eye also shall see my desire on mine enemies, and mine ears shall hear my desire of the wicked that rise up against me. |
12 ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል። |
12 The righteous shall flourish like the palm tree: he shall grow like a cedar in Lebanon. |
13 በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ። |
13 Those that be planted in the house of the Lord shall flourish in the courts of our God. |
14 ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ። |
14 They shall still bring forth fruit in old age; they shall be fat and flourishing; |
15 አምላኬ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ ይነግራሉ፥ በእርሱም ዘንድ ዓመፃ የለም። |
15 To shew that the Lord is upright: he is my rock, and there is no unrighteousness in him. |