ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #30
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 30

Exodus 30

1 የዕጣን መሠዊያውን ሥራ ከግራር እንጨት አድርገው።

1 And thou shalt make an altar to burn incense upon: of shittim wood shalt thou make it.

2 ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱም አንድ ክንድ፥ አራት ማዕዘን ይሁን ከፍታውም ሁለት ክንድ ይሆናል ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር በአንድነት የተሠሩ ይሁኑ።

2 A cubit shall be the length thereof, and a cubit the breadth thereof; foursquare shall it be: and two cubits shall be the height thereof: the horns thereof shall be of the same.

3 ላይኛውንና የግድግዳውንም ዙሪያ ቀንዶቹንም በጥሩ ወርቅ ትለብጠዋለህ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ታደርግለታለህ።

3 And thou shalt overlay it with pure gold, the top thereof, and the sides thereof round about, and the horns thereof; and thou shalt make unto it a crown of gold round about.

4 ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት። በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ ለመሸከምም የመሎጊያዎች ስፍራ ይሁኑ።

4 And two golden rings shalt thou make to it under the crown of it, by the two corners thereof, upon the two sides of it shalt thou make it; and they shall be for places for the staves to bear it withal.

5 መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት አድርግ፥ በወርቅም ለብጣቸው።

5 And thou shalt make the staves of shittim wood, and overlay them with gold.

6 በምስክሩ ታቦት አጠገብም ካለው መጋረጃ በፊት ታኖረዋለህ ይህንም አንተን በምገናኝበት ከምስክሩ በላይ ባለው በስርየት መክደኛ ፊት ታኖረዋለህ።

6 And thou shalt put it before the vail that is by the ark of the testimony, before the mercy seat that is over the testimony, where I will meet with thee.

7 አሮንም የጣፋጭ ሽቱ እጣን ይጠንበት በማለዳ በማለዳ መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው።

7 And Aaron shall burn thereon sweet incense every morning: when he dresseth the lamps, he shall burn incense upon it.

8 ይህን በእግዚአብሔር ፊት ለልጅ ልጃችሁ የዘወትር ዕጣን ይሆን ዘንድ አሮን በማታ ጊዜ መብራቶቹን ሲያበራ ያጥነዋል።

8 And when Aaron lighteth the lamps at even, he shall burn incense upon it, a perpetual incense before the Lord throughout your generations.

9 ሌላም ዕጣን፥ የሚቃጠለውንም መስዋዕት፥ የእህሉንም ቍርባን አታቀርብበትም የመጠጥም ቍርባን አታፈስስበትም።

9 Ye shall offer no strange incense thereon, nor burnt sacrifice, nor meat offering; neither shall ye pour drink offering thereon.

10 አሮንም በአመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል በአመት አንድ ጊዜ ለልጅ ልጃችሁ ማስተስረያ በሚሆን በኃጢአት መሥዋዕት ደም ማስተስረያ ያደርግበታል። ለእግዚአብሔር ቅድስተ ቅዱሳን ናት።

10 And Aaron shall make an atonement upon the horns of it once in a year with the blood of the sin offering of atonements: once in the year shall he make atonement upon it throughout your generations: it is most holy unto the Lord.

11 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

11 And the Lord spake unto Moses, saying,

12 አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።

12 When thou takest the sum of the children of Israel after their number, then shall they give every man a ransom for his soul unto the Lord, when thou numberest them; that there be no plague among them, when thou numberest them.

13 አልፎ የሚቈጠር ሁሉ ግማሽ ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ይሰጣል የሰቅል ግማሽ ለእግዚአብሔር ያነሣል።

13 This they shall give, every one that passeth among them that are numbered, half a shekel after the shekel of the sanctuary: (a shekel is twenty gerahs:) an half shekel shall be the offering of the Lord.

14 ሰቅሉ ሀያ ኦቦሊ ነው። አልፎ የተቈጠረ ሁሉ፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም ከፍ ያለ፥ የእግዚአብሔርን ስጦታ ይሰጣል።

14 Every one that passeth among them that are numbered, from twenty years old and above, shall give an offering unto the Lord.

15 ለነፍሳችሁ ማስተስረያ የእግዚአብሔርን ስጦታ ስትሰጡ ባለ ጠጋው ከሰቅል ግማሽ አይጨምር፥ ድሀውም አያጕድል።

15 The rich shall not give more, and the poor shall not give less than half a shekel, when they give an offering unto the Lord, to make an atonement for your souls.

16 የማስተስረያውንም ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለመገናኛው ድንኳን ማገልገያ ታደርገዋለህ በእግዚአብሔርም ፊት ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ይሁን።

16 And thou shalt take the atonement money of the children of Israel, and shalt appoint it for the service of the tabernacle of the congregation; that it may be a memorial unto the children of Israel before the Lord, to make an atonement for your souls.

17 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

17 And the Lord spake unto Moses, saying,

18 የመታጠቢያ ሰንና መቀመጫውን ከናስ ሥራ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል እርሱን አድርገህ ውኃን ትጨምርበታለህ።

18 Thou shalt also make a laver of brass, and his foot also of brass, to wash withal: and thou shalt put it between the tabernacle of the congregation and the altar, and thou shalt put water therein.

19 አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡበታል።

19 For Aaron and his sons shall wash their hands and their feet thereat:

20 ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት መስዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ፥ እንዳይሞቱ ይታጠቡበታል።

20 When they go into the tabernacle of the congregation, they shall wash with water, that they die not; or when they come near to the altar to minister, to burn offering made by fire unto the Lord:

21 እንዳይሞቱም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡ ይህም ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ የዘላለም ሥርዓት ይሆንላቸዋል።

21 So they shall wash their hands and their feet, that they die not: and it shall be a statute for ever to them, even to him and to his seed throughout their generations.

22 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

22 Moreover the Lord spake unto Moses, saying,

23 አንተም ክቡሩን ሽቱ ውሰድ የተመረጠ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽም ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥

23 Take thou also unto thee principal spices, of pure myrrh five hundred shekels, and of sweet cinnamon half so much, even two hundred and fifty shekels, and of sweet calamus two hundred and fifty shekels,

24 ብርጕድም አምስት መቶ ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የወይራ ዘይትም አንድ የኢን መስፈሪያ ትወስዳለህ።

24 And of cassia five hundred shekels, after the shekel of the sanctuary, and of oil olive an hin:

25 በቀማሚም ብልሃት እንደ ተሠራ ቅመም፥ የተቀደሰ የቅብዓት ዘይት ታደርገዋለህ የተቀደሰ የቅብዓት ዘይት ይሆናል።

25 And thou shalt make it an oil of holy ointment, an ointment compound after the art of the apothecary: it shall be an holy anointing oil.

26 የመገናኛውንም ድንኳን፥ የምስክሩንም ታቦት፥

26 And thou shalt anoint the tabernacle of the congregation therewith, and the ark of the testimony,

27 ገበታውንም ዕቃውንም ሁሉ፥ መቅረዙንም ዕቃውንም፥ የዕጣን መሠዊያውንም፥

27 And the table and all his vessels, and the candlestick and his vessels, and the altar of incense,

28 ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያና ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም ትቀባበታለህ።

28 And the altar of burnt offering with all his vessels, and the laver and his foot.

29 ሁሉንም ትቀድሳቸዋለህ፥ ቅድስተ ቅዱሳንም ይሆናሉ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።

29 And thou shalt sanctify them, that they may be most holy: whatsoever toucheth them shall be holy.

30 በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፥ ቀድሳቸውም።

30 And thou shalt anoint Aaron and his sons, and consecrate them, that they may minister unto me in the priest’s office.

31 አንተም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር። ይህ ለልጅ ልጃችሁ የተቀደሰ የቅብዓት ዘይት ይሁንልኝ።

31 And thou shalt speak unto the children of Israel, saying, This shall be an holy anointing oil unto me throughout your generations.

32 በሰው ሥጋ ላይ አይፍሰስ እንደ እርሱም የተሰራ ሌላ ቅብዓት አታድርጉ ቅዱስ ነው፥ ለእናንተም ቅዱስ ይሁን።

32 Upon man’s flesh shall it not be poured, neither shall ye make any other like it, after the composition of it: it is holy, and it shall be holy unto you.

33 እንደ እርሱ ያለውን የሚያደርግ ሰው፥ በሌላም ሰው ላይ የሚያፈስሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።

33 Whosoever compoundeth any like it, or whosoever putteth any of it upon a stranger, shall even be cut off from his people.

34 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም እጣን ውሰድ የሁሉም መጠን ትክክል ይሁን።

34 And the Lord said unto Moses, Take unto thee sweet spices, stacte, and onycha, and galbanum; these sweet spices with pure frankincense: of each shall there be a like weight:

35 በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ፥ በጨው የተቀመመ ንጹሕና ቅዱስ ዕጣን አድርገው።

35 And thou shalt make it a perfume, a confection after the art of the apothecary, tempered together, pure and holy:

36 ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታልመውማለህ ከዚያም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። እርሱም የቅዱሳን ቅዱስ ይሁንላችሁ።

36 And thou shalt beat some of it very small, and put of it before the testimony in the tabernacle of the congregation, where I will meet with thee: it shall be unto you most holy.

37 እንደ እርሱ የተሠራ ዕጣን ለእናንተ አታድርጉ በእናንተ ዘንድም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን።

37 And as for the perfume which thou shalt make, ye shall not make to yourselves according to the composition thereof: it shall be unto thee holy for the Lord.

38 ሊያሸትተውም እንደ እርሱ የሚያደርግ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።

38 Whosoever shall make like unto that, to smell thereto, shall even be cut off from his people.