ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #20
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘጸአት 20 |
Exodus 20 |
1 እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ። |
1 And God spake all these words, saying, |
2 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። |
2 I am the Lord thy God, which have brought thee out of the land of Egypt, out of the house of bondage. |
3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። |
3 Thou shalt have no other gods before me. |
4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። |
4 Thou shalt not make unto thee any graven image, or any likeness of any thing that is in heaven above, or that is in the earth beneath, or that is in the water under the earth: |
5 አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ |
5 Thou shalt not bow down thyself to them, nor serve them: for I the Lord thy God am a jealous God, visiting the iniquity of the fathers upon the children unto the third and fourth generation of them that hate me; |
6 ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። |
6 And shewing mercy unto thousands of them that love me, and keep my commandments. |
7 የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና። |
7 Thou shalt not take the name of the Lord thy God in vain; for the Lord will not hold him guiltless that taketh his name in vain. |
8 የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ። |
8 Remember the sabbath day, to keep it holy. |
9 ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ |
9 Six days shalt thou labour, and do all thy work: |
10 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ |
10 But the seventh day is the sabbath of the Lord thy God: in it thou shalt not do any work, thou, nor thy son, nor thy daughter, thy manservant, nor thy maidservant, nor thy cattle, nor thy stranger that is within thy gates: |
11 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም። |
11 For in six days the Lord made heaven and earth, the sea, and all that in them is, and rested the seventh day: wherefore the Lord blessed the sabbath day, and hallowed it. |
12 አባትህንና እናትህን አክብር እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም። |
12 Honour thy father and thy mother: that thy days may be long upon the land which the Lord thy God giveth thee. |
13 አትግደል። |
13 Thou shalt not kill. |
14 አታመንዝር። |
14 Thou shalt not commit adultery. |
15 አትስረቅ። |
15 Thou shalt not steal. |
16 በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር። |
16 Thou shalt not bear false witness against thy neighbour. |
17 የባልንጀራህን ቤት አትመኝ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ። |
17 Thou shalt not covet thy neighbour’s house, thou shalt not covet thy neighbour’s wife, nor his manservant, nor his maidservant, nor his ox, nor his ass, nor any thing that is thy neighbour’s. |
18 ሕዝቡም ሁሉ ነጐድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ ሕዝቡም ባዩ ጊዜ ተርበደበዱ፥ ርቀውም ቆሙ። |
18 And all the people saw the thunderings, and the lightnings, and the noise of the trumpet, and the mountain smoking: and when the people saw it, they removed, and stood afar off. |
19 ሙሴንም። አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን እንዳንሞት ግን እግዚአብሔር አይናገረን አሉት። |
19 And they said unto Moses, Speak thou with us, and we will hear: but let not God speak with us, lest we die. |
20 ሙሴም ለሕዝቡ። እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ፥ ኃጢአትንም እንዳትሠሩ እርሱን መፍራት በልባችሁ ይሆን ዘንድ መጥቶአልና አትፍሩ አለ። |
20 And Moses said unto the people, Fear not: for God is come to prove you, and that his fear may be before your faces, that ye sin not. |
21 ሕዝቡም ርቀው ቆሙ፥ ሙሴም እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጨለማው ቀረበ። |
21 And the people stood afar off, and Moses drew near unto the thick darkness where God was. |
22 እግዚአብሔር ሙሴን አለው። ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በል። እኔ ከሰማይ እንደ ተናገርኋችሁ እናንተ አይታችኋል። |
22 And the Lord said unto Moses, Thus thou shalt say unto the children of Israel, Ye have seen that I have talked with you from heaven. |
23 በአጠገቤ ምንም አታድርጉ የብር አማልክት የወርቅም አማልክት ለእናንተ አታድርጉ። |
23 Ye shall not make with me gods of silver, neither shall ye make unto you gods of gold. |
24 የጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፥ የሚቃጠለውንና የደኅንነት መሥዋዕትህን በጎችህንም በሬዎችህንም ሠዋበት ስሜን በማሳስብበት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባርክሃለሁ። |
24 An altar of earth thou shalt make unto me, and shalt sacrifice thereon thy burnt offerings, and thy peace offerings, thy sheep, and thine oxen: in all places where I record my name I will come unto thee, and I will bless thee. |
25 የድንጋይም መሠዊያ ብታደርግልኝ ብረት በነካው ድንጋይ አትሥራው በመሣሪያ ብትነካው ታረክሰዋለህና። |
25 And if thou wilt make me an altar of stone, thou shalt not build it of hewn stone: for if thou lift up thy tool upon it, thou hast polluted it. |
26 ኃፍረተ ሥጋህ በእርሱ እንዳይገለጥ ወደ መሠዊያዬ በደረጃ አትውጣ። |
26 Neither shalt thou go up by steps unto mine altar, that thy nakedness be not discovered thereon. |