ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #13
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 13

Leviticus 13

1 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው።

1 And the Lord spake unto Moses and Aaron, saying,

2 ማናቸውም ሰው በሥጋው ቁርበት ላይ እባጭ ወይም ብጕር ወይም ቋቁቻ ቢታይ፥ በሥጋው ቁርበት እንደ ለምጽ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።

2 When a man shall have in the skin of his flesh a rising, a scab, or bright spot, and it be in the skin of his flesh like the plague of leprosy; then he shall be brought unto Aaron the priest, or unto one of his sons the priests:

3 ካህኑም በሥጋው ቁርበት ያለውን ደዌ ያያል ጠጕሩም ተለውጦ ቢነጣ ደዌውም ወደ ሥጋው ቁርበት ቢጠልቅ፥ እርሱ የለምጽ ደዌ ነው ካህኑም አይቶ። ርኩስ ነው ይበለው።

3 And the priest shall look on the plague in the skin of the flesh: and when the hair in the plague is turned white, and the plague in sight be deeper than the skin of his flesh, it is a plague of leprosy: and the priest shall look on him, and pronounce him unclean.

4 ቋቁቻውም በሥጋው ቁርበት ላይ ቢነጣ፥ ከቁርበቱም የጠለቀ ባይመስል፥ ጠጕሩም ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይዘጋበታል።

4 If the bright spot be white in the skin of his flesh, and in sight be not deeper than the skin, and the hair thereof be not turned white; then the priest shall shut up him that hath the plague seven days:

5 በሰባተኛውም ቀን ካህኑ ያየዋል እነሆም፥ ደዌው በዓይኑ ፊት እንደ ነበረ ቢሆን፥ በቁርበቱም ላይ ባይሰፋ፥ ካህኑ ሰባት ቀን ደግሞ ይዘጋበታል።

5 And the priest shall look on him the seventh day: and, behold, if the plague in his sight be at a stay, and the plague spread not in the skin; then the priest shall shut him up seven days more:

6 ደግሞ በሰባተኛው ቀን ካህኑ ያየዋል እነሆም፥ ደዌው ቢከስም፥ ደዌውም በቁርበቱ ላይ ባይሰፋ፥ ካህኑ። ንጹሕ ነው ይለዋል እከክ ነው ልብሱንም አጥቦ ንጹሕ ይሆናል።

6 And the priest shall look on him again the seventh day: and, behold, if the plague be somewhat dark, and the plague spread not in the skin, the priest shall pronounce him clean: it is but a scab: and he shall wash his clothes, and be clean.

7 ስለ መንጻቱ በካህኑ ዘንድ ከታየ በኋላ እከኩ በቁርበቱ ላይ ቢሰፋ፥ እንደ ገና ሊታይ ወደ ካህኑ ይቀርባል።

7 But if the scab spread much abroad in the skin, after that he hath been seen of the priest for his cleansing, he shall be seen of the priest again:

8 ካህኑም ያያል እነሆም፥ እከኩ በቁርበቱ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ። ርኩስ ነው ይለዋል ለምጽ ነው።

8 And if the priest see that, behold, the scab spreadeth in the skin, then the priest shall pronounce him unclean: it is a leprosy.

9 የለምጽ ደዌ በሰው ውስጥ ቢሆን እርሱን ወደ ካህኑ ያመጡለታል።

9 When the plague of leprosy is in a man, then he shall be brought unto the priest;

10 ካህኑም ያያል እነሆም፥ በቁርበቱ ላይ ነጭ እባጭ ቢሆን፥ ጠጕሩም ተለውጦ ቢነጣ፥ ሥጋውም በእባጩ ውስጥ ቢያዥ፥

10 And the priest shall see him: and, behold, if the rising be white in the skin, and it have turned the hair white, and there be quick raw flesh in the rising;

11 እርሱ በሥጋው ቁርበት ላይ አሮጌ ለምጽ ነው፥ ካህኑም። ርኩስ ነው ይለዋል እርሱ ርኩስ ነውና አይዘጋበትም።

11 It is an old leprosy in the skin of his flesh, and the priest shall pronounce him unclean, and shall not shut him up: for he is unclean.

12 ለምጹም በቁርበቱ ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ለምጹም የታመመውን ሰው ቁርበቱን ሁሉ ከራሱ እስከ እግሮቹ ድረስ እንደ ከደነው ለካህኑ ቢመስለው፥ ካህኑ ያያል

12 And if a leprosy break out abroad in the skin, and the leprosy cover all the skin of him that hath the plague from his head even to his foot, wheresoever the priest looketh;

13 እነሆም፥ ለምጹ ሥጋውን ሁሉ ቢከድን የታመመውን ሰው። ንጹሕ ነው ይለዋል ሥጋው ሁሉ ፈጽሞ ተለውጦ ነጭ ሆኖአል ንጹሕ ነው።

13 Then the priest shall consider: and, behold, if the leprosy have covered all his flesh, he shall pronounce him clean that hath the plague: it is all turned white: he is clean.

14 የሚያዠው ሥጋ ግን ሲታይበት ርኩስ ይሆናል።

14 But when raw flesh appeareth in him, he shall be unclean.

15 ካህኑም የሚያዠውን ሥጋ አይቶ። ርኩስ ነው ይለዋል የሚያዠው ሥጋ ለምጽ ነውና ርኩስ ነው።

15 And the priest shall see the raw flesh, and pronounce him to be unclean: for the raw flesh is unclean: it is a leprosy.

16 የሚያዠውም ሥጋ ተለውጦ ቢነጣ እንደ ገና ወደ ካህኑ ይመጣል።

16 Or if the raw flesh turn again, and be changed unto white, he shall come unto the priest;

17 ካህኑም ያየዋል እነሆም፥ ደዌው ቢነጣ ካህኑ የታመመውን፦ ንጹሕ ነው ይለዋል ንጹሕ ነው።

17 And the priest shall see him: and, behold, if the plague be turned into white; then the priest shall pronounce him clean that hath the plague: he is clean.

18 በሥጋውም ቁርበት ላይ ቍስል ቢሆንና ቢሽር፥

18 The flesh also, in which, even in the skin thereof, was a boil, and is healed,

19 በቍስሉም ስፍራ ነጭ እባጭ ወይም ቀላ ያለ ቋቁቻ ቢወጣ፥ በካህኑ ዘንድ ይታያል።

19 And in the place of the boil there be a white rising, or a bright spot, white, and somewhat reddish, and it be shewed to the priest;

20 ካህኑም ያያል እነሆም፥ ወደ ቁርበቱ ውስጥ ጠልቆ ቢታይ፥ ጠጕሩም ተለውጦ ቢነጣ፥ ካህኑ። ርኩስ ነው ይለዋል የለምጽ ደዌ ነው ከቍስሉ ውስጥ ወጥቶአል።

20 And if, when the priest seeth it, behold, it be in sight lower than the skin, and the hair thereof be turned white; the priest shall pronounce him unclean: it is a plague of leprosy broken out of the boil.

21 ካህኑም ቢያየው፥ ነጭም ጠጕር ባይኖርበት፥ ወደ ቁርበቱም ውስጥ ባይጠልቅ ነገር ግን ቢከስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይዘጋበታል።

21 But if the priest look on it, and, behold, there be no white hairs therein, and if it be not lower than the skin, but be somewhat dark; then the priest shall shut him up seven days:

22 በቁርበቱም ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ። ርኩስ ነው ይለዋል ደዌ ነው።

22 And if it spread much abroad in the skin, then the priest shall pronounce him unclean: it is a plague.

23 ቋቁቻው ግን በስፍራው ቢቆም ባይሰፋም፥ የቍስል ጠባሳ ነው ካህኑም። ንጹሕ ነው ይለዋል።

23 But if the bright spot stay in his place, and spread not, it is a burning boil; and the priest shall pronounce him clean.

24 በሥጋውም ቁርበት የእሳት ትኵሳት ቢኖርበት፥ በተቃጠለውም ስፍራ ነጭ ወይም ቀላ ያለ ቋቁቻ ቢታይ፥

24 Or if there be any flesh, in the skin whereof there is a hot burning, and the quick flesh that burneth have a white bright spot, somewhat reddish, or white;

25 ካህኑ ያየዋል እነሆም፥ በቋቁቻው ጠጕሩ ተለውጦ ቢነጣ፥ ወደ ቁርበቱም ውስጥ ቢጠልቅ፥ ለምጽ ነው ከተቃጠለውም ስፍራ ወጥቶአል ካህኑም። ርኩስ ነው ይለዋል የለምጽ ደዌ ነው።

25 Then the priest shall look upon it: and, behold, if the hair in the bright spot be turned white, and it be in sight deeper than the skin; it is a leprosy broken out of the burning: wherefore the priest shall pronounce him unclean: it is the plague of leprosy.

26 ካህኑም ቢያየው፥ በቋቁቻውም ነጭ ጠጕር ባይኖር፥ ወደ ቁርበቱም ባይጠልቅ ነገር ግን ቢከስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይዘጋበታል።

26 But if the priest look on it, and, behold, there be no white hair in the bright spot, and it be no lower than the other skin, but be somewhat dark; then the priest shall shut him up seven days:

27 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ያየዋል በቁርበቱም ላይ ቢሰፋ ካህኑ። ርኩስ ነው ይለዋል የለምጽ ደዌ ነው።

27 And the priest shall look upon him the seventh day: and if it be spread much abroad in the skin, then the priest shall pronounce him unclean: it is the plague of leprosy.

28 ቋቁቻውም በስፍራው ላይ ቢቆም፥ በቁርበቱም ላይ ባይሰፋ ነገር ግን ቢከስም፥ የትኵሳት እባጭ ነው የትኵሳትም ጠባሳ ነውና ካህኑ። ንጹሕ ነው ይለዋል።

28 And if the bright spot stay in his place, and spread not in the skin, but it be somewhat dark; it is a rising of the burning, and the priest shall pronounce him clean: for it is an inflammation of the burning.

29 ማናቸውም ወንድ ወይም ሴት በራሱ ወይም በአገጩ ደዌ ቢኖርበት፥

29 If a man or woman have a plague upon the head or the beard;

30 ካህኑ ደዌውን ያያል እነሆም፥ ወደ ቁርበቱ ቢጠልቅ፥ በውስጡም ቀጭን ብጫ ጠጕር ቢኖርበት፥ ካህኑ። ርኩስ ነው ይለዋል ቈረቈር ነው የራስ ወይም የአገጭ ለምጽ ነው።

30 Then the priest shall see the plague: and, behold, if it be in sight deeper than the skin; and there be in it a yellow thin hair; then the priest shall pronounce him unclean: it is a dry scall, even a leprosy upon the head or beard.

31 ካህኑም የቈረቈሩን ደዌ ቢያይ፥ ወደ ቁርበቱም ባይጠልቅ፥ ጥቁርም ጠጕር ባይኖርበት፥ ካህኑ የቈረቈር ደዌ ያለበትን ሰው ሰባት ቀን ይዘጋበታል።

31 And if the priest look on the plague of the scall, and, behold, it be not in sight deeper than the skin, and that there is no black hair in it; then the priest shall shut up him that hath the plague of the scall seven days:

32 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ደዌውን ያያል እነሆም፥ ቈረቈሩ ባይሰፋ፥ በውስጡም ብጫ ጠጕር ባይኖር፥ የቈረቈሩም መልክ ወደ ቁርበቱ ባይጠልቅ፥ ይላጫል፥

32 And in the seventh day the priest shall look on the plague: and, behold, if the scall spread not, and there be in it no yellow hair, and the scall be not in sight deeper than the skin;

33 ቈረቈሩ ግን አይላጭም ካህኑም ቈረቈር ያለበትን ሰው ሰባት ቀን ደግሞ ይዘጋበታል።

33 He shall be shaven, but the scall shall he not shave; and the priest shall shut up him that hath the scall seven days more:

34 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቈረቈሩን ያያል እነሆም፥ ቈረቈሩ በቁርበቱ ላይ ባይሰፋ፥ መልኩም ወደ ቁርበቱ ባይጠልቅ፥ ካህኑ። ንጹሕ ነው ይለዋል ልብሱን አጥቦ ንጹሕ ይሆናል።

34 And in the seventh day the priest shall look on the scall: and, behold, if the scall be not spread in the skin, nor be in sight deeper than the skin; then the priest shall pronounce him clean: and he shall wash his clothes, and be clean.

35 ከነጻ በኋላ ግን ቈረቈሩ በቁርበቱ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ያየዋል

35 But if the scall spread much in the skin after his cleansing;

36 እነሆም፥ ቈረቈሩ በቁርበቱ ላይ ቢሰፋ ካህኑ ብጫውን ጠጕር አይፈልግም ርኩስ ነው።

36 Then the priest shall look on him: and, behold, if the scall be spread in the skin, the priest shall not seek for yellow hair; he is unclean.

37 ቈረቈሩ ግን በዓይኑ ፊት እንደ ነበረ ቢሆን፥ ጥቁርም ጠጕር ቢበቅልበት፥ ቈረቈሩ ሽሮአል እርሱም ንጹሕ ነው ካህኑም። ንጹሕ ነው ይለዋል።

37 But if the scall be in his sight at a stay, and that there is black hair grown up therein; the scall is healed, he is clean: and the priest shall pronounce him clean.

38 ማናቸውም ወንድ ወይም ሴት በሥጋው ቁርበት ላይ ነጭ ቋቁቻ ቢኖርበት፥

38 If a man also or a woman have in the skin of their flesh bright spots, even white bright spots;

39 ካህኑ ያያል እነሆም፥ በሥጋቸው ቁርበት ላይ ያለው ቋቁቻ ፈገግ ቢል አጓጐት ነው ከቁርበቱ ውስጥ ወጥቶአል ንጹሕ ነው።

39 Then the priest shall look: and, behold, if the bright spots in the skin of their flesh be darkish white; it is a freckled spot that groweth in the skin; he is clean.

40 የሰውም ጠጕር ከራሱ ቢመለጥ እርሱ ቡሀ ነው ነገር ግን ንጹሕ ነው።

40 And the man whose hair is fallen off his head, he is bald; yet is he clean.

41 ጠጕሩም ከግምባሩ ቢመለጥ እርሱ ራሰ በራ ነው ነገር ግን ንጹሕ ነው።

41 And he that hath his hair fallen off from the part of his head toward his face, he is forehead bald: yet is he clean.

42 በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ነጭ ወይም ቀላ ያለ ደዌ ቢኖርበት፥ እርሱ ከቡሀነቱ ወይም ከራሰ በራነቱ የወጣ ለምጽ ነው።

42 And if there be in the bald head, or bald forehead, a white reddish sore; it is a leprosy sprung up in his bald head, or his bald forehead.

43 ካህኑም ያየዋል እነሆም፥ የደዌው እብጠት፥ በሥጋው ቁርበት ላይ የሆነ ለምጽ መስሎ፥ በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ነጭ ወይም ቀላ ያለ ቢሆን፥

43 Then the priest shall look upon it: and, behold, if the rising of the sore be white reddish in his bald head, or in his bald forehead, as the leprosy appeareth in the skin of the flesh;

44 ለምጻም ሰው ነው ርኩስ ነው ካህኑ። በእርግጥ ርኩስ ነው ይለዋል ደዌው በራሱ ነው።

44 He is a leprous man, he is unclean: the priest shall pronounce him utterly unclean; his plague is in his head.

45 የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥ ራሱም የተገለጠ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን ርኩስ ርኩስ ነኝ ይበል።

45 And the leper in whom the plague is, his clothes shall be rent, and his head bare, and he shall put a covering upon his upper lip, and shall cry, Unclean, unclean.

46 ደዌው ባለበት ዘመን ሁሉ ርኩስ ይሆናል እርሱ ርኩስ ነው ብቻውን ይቀመጣል መኖሪያውም ከሰፈር በውጭ ይሆናል።

46 All the days wherein the plague shall be in him he shall be defiled; he is unclean: he shall dwell alone; without the camp shall his habitation be.

47 የለምጽም ደዌ በልብስ ላይ ቢሆን፥ ልብሱም የበግ ጠጕር ወይም በፍታ ቢሆን፥

47 The garment also that the plague of leprosy is in, whether it be a woollen garment, or a linen garment;

48 በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ በፍታ ወይም የበግ ጠጕር ቢሆን፥ አጐዛ ወይም ከአጐዛ የሚደረግ ነገር ቢሆን፥

48 Whether it be in the warp, or woof; of linen, or of woollen; whether in a skin, or in any thing made of skin;

49 ደዌው በልብሱ ወይም በአጐዛው ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛው በሚደረገው ነገር አረንጓዴ ወይም ቀይ ቢሆን፥ የለምጽ ደዌ ነው ለካህኑ ይታያል።

49 And if the plague be greenish or reddish in the garment, or in the skin, either in the warp, or in the woof, or in any thing of skin; it is a plague of leprosy, and shall be shewed unto the priest:

50 ካህኑም ደዌውን አይቶ ደዌው ያለበትን ነገር ሰባት ቀን ይዘጋበታል።

50 And the priest shall look upon the plague, and shut up it that hath the plague seven days:

51 በሰባተኛውም ቀን ደዌውን ያያል ደዌውም በልብስ ላይ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም በአጐዛው ወይም ከአጐዛው በሚደረግ ነገር ቢሰፋ፥ ደዌው እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነው ርኩስ ነው።

51 And he shall look on the plague on the seventh day: if the plague be spread in the garment, either in the warp, or in the woof, or in a skin, or in any work that is made of skin; the plague is a fretting leprosy; it is unclean.

52 ልብሱን ያቃጥል ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጕር ወይም በፍታ ቢሆን ወይም ከአጐዛው የተደረገ ቢሆን፥ ደዌ ያለበት ሁሉ፥ እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነውና በእሳት ይቃጠል።

52 He shall therefore burn that garment, whether warp or woof, in woollen or in linen, or any thing of skin, wherein the plague is: for it is a fretting leprosy; it shall be burnt in the fire.

53 ካህኑ ቢያይ፥ እነሆም፥ ደዌው በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛ በተደረገ ነገር ቢሆን በልብሱ ላይ ባይሰፋ፥

53 And if the priest shall look, and, behold, the plague be not spread in the garment, either in the warp, or in the woof, or in any thing of skin;

54 ካህኑ ደዌ ያለበቱ ነገር እንዲታጠብ ይዘዝ ሌላም ሰባት ቀን ይዘጋበታል።

54 Then the priest shall command that they wash the thing wherein the plague is, and he shall shut it up seven days more:

55 ደዌውም ከታጠበ በኋላ ካህኑ ያያል እነሆም፥ ደዌው መልኩን ባይለውጥ ባይሰፋም፥ ርኩስ ነው በእሳት አቃጥለው ምልክቱ በውስጥ ወይም በውጭ ቢሆን እየፋገ የሚሄድ ደዌ ነው።

55 And the priest shall look on the plague, after that it is washed: and, behold, if the plague have not changed his colour, and the plague be not spread; it is unclean; thou shalt burn it in the fire; it is fret inward, whether it be bare within or without.

56 ካህኑም ቢያይ፥ እነሆም፥ ደዌው ከታጠበ በኋላ ቢከስም፥ ከልብሱ ወይም ከአጐዛው ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ይቅደደው።

56 And if the priest look, and, behold, the plague be somewhat dark after the washing of it; then he shall rend it out of the garment, or out of the skin, or out of the warp, or out of the woof:

57 በልብሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛው በተደረገ ነገር ላይ ደግሞ ቢታይ፥ የወጣ ለምጽ ነው ደዌው ያለበትን ነገር አቃጥለው።

57 And if it appear still in the garment, either in the warp, or in the woof, or in any thing of skin; it is a spreading plague: thou shalt burn that wherein the plague is with fire.

58 አንተም ካጠብኸው ልብስ ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ወይም ከአጐዛው ከተደረገው ነገር ላይ ደዌው ቢጠፋ፥ ሁለተኛ ጊዜ ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል።

58 And the garment, either warp, or woof, or whatsoever thing of skin it be, which thou shalt wash, if the plague be departed from them, then it shall be washed the second time, and shall be clean.

59 በበግ ጠጕር ልብስ ወይም በበፍታ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛ በተደረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።

59 This is the law of the plague of leprosy in a garment of woollen or linen, either in the warp, or woof, or any thing of skins, to pronounce it clean, or to pronounce it unclean.