ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #17
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘኍልቍ 17 |
Numbers 17 |
1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
1 And the Lord spake unto Moses, saying, |
2 ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፥ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸው ከየአባቶቻቸው ቤት አሥራ ሁለት በትሮች፥ ውሰድ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ። |
2 Speak unto the children of Israel, and take of every one of them a rod according to the house of their fathers, of all their princes according to the house of their fathers twelve rods: write thou every man’s name upon his rod. |
3 አንድ በትርም ለአባቶቻቸው ቤት አለቃ ይሆናልና በሌዊ በትር ላይ የአሮንን ስም ጻፍ። |
3 And thou shalt write Aaron’s name upon the rod of Levi: for one rod shall be for the head of the house of their fathers. |
4 እኔ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት አኑራቸው። |
4 And thou shalt lay them up in the tabernacle of the congregation before the testimony, where I will meet with you. |
5 እንዲህም ይሆናል የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቁጣለች በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ። |
5 And it shall come to pass, that the man’s rod, whom I shall choose, shall blossom: and I will make to cease from me the murmurings of the children of Israel, whereby they murmur against you. |
6 ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገራቸው አለቆቻቸው ሁሉ አሥራ ሁለት በትሮች፥ እያንዳንዱም አለቃ በየአባቱ ቤት አንድ አንድ በትር፥ ሰጡት የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። |
6 And Moses spake unto the children of Israel, and every one of their princes gave him a rod apiece, for each prince one, according to their fathers’ houses, even twelve rods: and the rod of Aaron was among their rods. |
7 ሙሴም በትሮቹን በእግዚአብሔር ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው። |
7 And Moses laid up the rods before the Lord in the tabernacle of witness. |
8 እንዲህም ሆነ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፥ ለመለመችም፥ አበባም አወጣች፥ የበሰለ ለውዝም አፈራች። |
8 And it came to pass, that on the morrow Moses went into the tabernacle of witness; and, behold, the rod of Aaron for the house of Levi was budded, and brought forth buds, and bloomed blossoms, and yielded almonds. |
9 ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው እነርሱም አዩ፥ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ። |
9 And Moses brought out all the rods from before the Lord unto all the children of Israel: and they looked, and took every man his rod. |
10 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልስ ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ እነርሱም እንዳይሞቱ ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ አለው። |
10 And the Lord said unto Moses, Bring Aaron’s rod again before the testimony, to be kept for a token against the rebels; and thou shalt quite take away their murmurings from me, that they die not. |
11 ሙሴም እንዲሁ አደረገ እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንዲሁ አደረገ። |
11 And Moses did so: as the Lord commanded him, so did he. |
12 የእስራኤልም ልጆች ሙሴን፦እነሆ፥ እንሞታለን፥ እንጠፋለን፥ ሁላችንም እንጠፋለን። |
12 And the children of Israel spake unto Moses, saying, Behold, we die, we perish, we all perish. |
13 የሚቀርብ ሁሉ፥ ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚቀርብ፥ ይሞታል በውኑ ሁላችን እንሞታለንን? ብለው ተናገሩት። |
13 Whosoever cometh any thing near unto the tabernacle of the Lord shall die: shall we be consumed with dying? |