ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #19
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 19

Leviticus 19

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።

2 Speak unto all the congregation of the children of Israel, and say unto them, Ye shall be holy: for I the Lord your God am holy.

3 ከእናንተ ሰው ሁሉ እናቱንና አባቱን ይፍራ፥ ሰንበታቴንም ጠብቁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

3 Ye shall fear every man his mother, and his father, and keep my sabbaths: I am the Lord your God.

4 ወደ ጣዖታትም ዘወር አትበሉ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም የአማልክት ምስሎች ለእናንተ አታድርጉ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

4 Turn ye not unto idols, nor make to yourselves molten gods: I am the Lord your God.

5 የደኅንነትንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ስትሰዉ እርሱን ደስ እንድታሰኙበት ሠዉት።

5 And if ye offer a sacrifice of peace offerings unto the Lord, ye shall offer it at your own will.

6 በምትሠዉት ቀንና በነጋው ይበላል እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል።

6 It shall be eaten the same day ye offer it, and on the morrow: and if ought remain until the third day, it shall be burnt in the fire.

7 በሦስተኛውም ቀን ቢበላ ጸያፍ ነው፥ ደስም አያሰኝም

7 And if it be eaten at all on the third day, it is abominable; it shall not be accepted.

8 የበላውም ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና ኃጢአቱን ይሸከማል ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።

8 Therefore every one that eateth it shall bear his iniquity, because he hath profaned the hallowed thing of the Lord: and that soul shall be cut off from among his people.

9 የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር ፈጽማችሁ አትጨዱ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ።

9 And when ye reap the harvest of your land, thou shalt not wholly reap the corners of thy field, neither shalt thou gather the gleanings of thy harvest.

10 የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

10 And thou shalt not glean thy vineyard, neither shalt thou gather every grape of thy vineyard; thou shalt leave them for the poor and stranger: I am the Lord your God.

11 አትስረቁ፥ አትካዱም፥ ከእናንተም እርስ በርሳችሁ ሐሰት አትነጋገሩ።

11 Ye shall not steal, neither deal falsely, neither lie one to another.

12 በስሜም በሐሰት አትማሉ፥ የአምላካችሁንም ስም አታርክሱ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

12 And ye shall not swear by my name falsely, neither shalt thou profane the name of thy God: I am the Lord.

13 በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። የሞያተኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አይደርብህ።

13 Thou shalt not defraud thy neighbour, neither rob him: the wages of him that is hired shall not abide with thee all night until the morning.

14 ደንቆሮውን አትስደብ፥ በዕውርም ፊት ዕንቅፋት አታድርግ፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

14 Thou shalt not curse the deaf, nor put a stumblingblock before the blind, but shalt fear thy God: I am the Lord.

15 በፍርድ ዓመፃ አታድርጉ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር ነገር ግን ለባልንጀራህ በእውነት ፍረድ።

15 Ye shall do no unrighteousness in judgment: thou shalt not respect the person of the poor, nor honour the person of the mighty: but in righteousness shalt thou judge thy neighbour.

16 በሕዝብህ መካከል በሸንጋይነት አትዙር በባልንጀራህም ደም ላይ አትቁም እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

16 Thou shalt not go up and down as a talebearer among thy people: neither shalt thou stand against the blood of thy neighbour: I am the Lord.

17 ወንድምህን በልብህ አትጥላው በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ ገሥጸው።

17 Thou shalt not hate thy brother in thine heart: thou shalt in any wise rebuke thy neighbour, and not suffer sin upon him.

18 አትበቀልም፥ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

18 Thou shalt not avenge, nor bear any grudge against the children of thy people, but thou shalt love thy neighbour as thyself: I am the Lord.

19 ሥርዓቴን ጠብቁ። እንስሳህ ከሌላ ዓይነት ጋር አይደባለቅ በእርሻህም ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።

19 Ye shall keep my statutes. Thou shalt not let thy cattle gender with a diverse kind: thou shalt not sow thy field with mingled seed: neither shall a garment mingled of linen and woollen come upon thee.

20 ማናቸውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥ እርስዋም ለባል የተሰጠች ዋጋዋም ያልተከፈለ አርነት ያልወጣች ብትሆን፥ ቅጣት አለባቸው አርነት አልወጣችምና አይገደሉም።

20 And whosoever lieth carnally with a woman, that is a bondmaid, betrothed to an husband, and not at all redeemed, nor freedom given her; she shall be scourged; they shall not be put to death, because she was not free.

21 እርሱም የበደሉን መሥዋዕት ይዞ ወደ እግዚአብሔር ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይመጣል፥ ለበደልም መሥዋዕት አውራ በግ ያመጣል።

21 And he shall bring his trespass offering unto the Lord, unto the door of the tabernacle of the congregation, even a ram for a trespass offering.

22 ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት በበደል መሥዋዕት በግ ያስተሰርይለታል የሠራውም ኃጢአት ይቀርለታል።

22 And the priest shall make an atonement for him with the ram of the trespass offering before the Lord for his sin which he hath done: and the sin which he hath done shall be forgiven him.

23 ወደ አገሩም በገባችሁ ጊዜ፥ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁም ጊዜ፥ ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ ሦስት ዓመት እንዳልተገረዘ ይሆንላችኋል አይበላም።

23 And when ye shall come into the land, and shall have planted all manner of trees for food, then ye shall count the fruit thereof as uncircumcised: three years shall it be as uncircumcised unto you: it shall not be eaten of.

24 የአራተኛውም ዓመት ፍሬ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ቅዱስ ይሁን።

24 But in the fourth year all the fruit thereof shall be holy to praise the Lord withal.

25 ፍሬውም ይበዛላችሁ ዘንድ የአምስተኛውን ዓመት ፍሬ ብሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

25 And in the fifth year shall ye eat of the fruit thereof, that it may yield unto you the increase thereof: I am the Lord your God.

26 ከደሙ ጋር ምንም አትብሉ አስማትም አታድርጉ፥ ሞራ ገላጭም አትሁኑ።

26 Ye shall not eat any thing with the blood: neither shall ye use enchantment, nor observe times.

27 የራስ ጠጕራችሁንም ዙሪያውን አትከርክሙት፥ ጢማችሁንም ዙሪያውን አትቍረጡት።

27 Ye shall not round the corners of your heads, neither shalt thou mar the corners of thy beard.

28 ስለ ሞተውም ሥጋችሁን አትንጩ፥ ገላችሁንም አትንቀሱት እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

28 Ye shall not make any cuttings in your flesh for the dead, nor print any marks upon you: I am the Lord.

29 ምድሪቱ ከግልሙትና ከርኵሰትም እንዳትሞላ ሴት ልጅህን ታመነዝር ዘንድ አታርክሳት።

29 Do not prostitute thy daughter, to cause her to be a whore; lest the land fall to whoredom, and the land become full of wickedness.

30 ሰንበታቴን ጠብቁ፥ መቅደሴንም አክብሩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

30 Ye shall keep my sabbaths, and reverence my sanctuary: I am the Lord.

31 ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

31 Regard not them that have familiar spirits, neither seek after wizards, to be defiled by them: I am the Lord your God.

32 በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

32 Thou shalt rise up before the hoary head, and honour the face of the old man, and fear thy God: I am the Lord.

33 በአገራችሁ ውስጥ ከእናንተ ጋር እንግዳ ቢቀመጥ ግፍ አታድርጉበት።

33 And if a stranger sojourn with thee in your land, ye shall not vex him.

34 እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገር ልጅ ይሁንላችሁ፥ እርሱንም እንደ ራስህ ውደድ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

34 But the stranger that dwelleth with you shall be unto you as one born among you, and thou shalt love him as thyself; for ye were strangers in the land of Egypt: I am the Lord your God.

35 በፍርድ፥ በመለካትም፥ በመመዘንም፥ በመስፈርም ዓመፃ አታድርጉ።

35 Ye shall do no unrighteousness in judgment, in meteyard, in weight, or in measure.

36 የእውነትም ሚዛን፥ የእውነትም መመዘኛ፥ የእውነትም የኢፍ መስፈሪያ፥ የእውነትም የኢን መስፈሪያ ይሁንላችሁ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ ነኝ።

36 Just balances, just weights, a just ephah, and a just hin, shall ye have: I am the Lord your God, which brought you out of the land of Egypt.

37 ሥርዓቴን ሁሉ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ አድርጉም እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

37 Therefore shall ye observe all my statutes, and all my judgments, and do them: I am the Lord.