ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #26
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 26

Leviticus 26

1 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።

1 Ye shall make you no idols nor graven image, neither rear you up a standing image, neither shall ye set up any image of stone in your land, to bow down unto it: for I am the Lord your God.

2 ሰንበታቴን ጠብቁ፥ መቅደሴንም ፍሩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

2 Ye shall keep my sabbaths, and reverence my sanctuary: I am the Lord.

3 በሥርዓቴ ብትሄዱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉትም፥

3 If ye walk in my statutes, and keep my commandments, and do them;

4 ዝናባችሁን በወቅቱ አዘንባለሁ፥ ምድሪቱም እህልዋን ትሰጣለች፥ የሜዳው ዛፎችም ፍሬአቸውን ይሰጣሉ።

4 Then I will give you rain in due season, and the land shall yield her increase, and the trees of the field shall yield their fruit.

5 የእህሉም ማበራየት በእናንተ ዘንድ እስከ ወይኑ መቍረጥ ይደርሳል፥ የወይኑም መቍረጥ እስከ እህሉ መዝራት ይደርሳል እስክትጠግቡም ድረስ እንጀራችሁን ትበላላችሁ፥ በምድራችሁም ላይ በጸጥታ ትኖራላችሁ።

5 And your threshing shall reach unto the vintage, and the vintage shall reach unto the sowing time: and ye shall eat your bread to the full, and dwell in your land safely.

6 በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራችሁ ትተኛላችሁ ክፉዎችንም አራዊት ከምድራችሁ አጠፋለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።

6 And I will give peace in the land, and ye shall lie down, and none shall make you afraid: and I will rid evil beasts out of the land, neither shall the sword go through your land.

7 ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ።

7 And ye shall chase your enemies, and they shall fall before you by the sword.

8 ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፥ መቶውም አሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።

8 And five of you shall chase an hundred, and an hundred of you shall put ten thousand to flight: and your enemies shall fall before you by the sword.

9 ፊቴም ወደ እናንተ ይሆናል፥ እንድታፈሩም አደርጋችኋለሁ፥ አበዛችሁማለሁ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።

9 For I will have respect unto you, and make you fruitful, and multiply you, and establish my covenant with you.

10 ብዙ ጊዜ የተቀመጠውንም አሮጌውን እህል ትበላላችሁ ከአዲሱም በፊት አሮጌውን ታወጣላችሁ።

10 And ye shall eat old store, and bring forth the old because of the new.

11 ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ ነፍሴም አትጸየፋችሁም።

11 And I will set my tabernacle among you: and my soul shall not abhor you.

12 በመካከላችሁም እሄዳለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፥ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ።

12 And I will walk among you, and will be your God, and ye shall be my people.

13 ባሪያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።

13 I am the Lord your God, which brought you forth out of the land of Egypt, that ye should not be their bondmen; and I have broken the bands of your yoke, and made you go upright.

14 ነገር ግን ባትሰሙኝ፥ እነዚህንም ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥

14 But if ye will not hearken unto me, and will not do all these commandments;

15 ሥርዓቴንም ብትንቁ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ እንዳታደርጉ፥ ቃል ኪዳኔንም እንድታፈርሱ ነፍሳችሁ ፍርዴን ብትጸየፍ፥

15 And if ye shall despise my statutes, or if your soul abhor my judgments, so that ye will not do all my commandments, but that ye break my covenant:

16 እኔም እንዲህ አደርግባችኋለሁ ፍርሃትን፥ ክሳትንም፥ ዓይናችሁንም የሚያፈዝዝ፥ ሰውነታችሁንም የሚያማስን ትኩሳት አወርድባችኋለሁ ዘራችሁንም በከንቱ ትዘራላችሁ፥ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።

16 I also will do this unto you; I will even appoint over you terror, consumption, and the burning ague, that shall consume the eyes, and cause sorrow of heart: and ye shall sow your seed in vain, for your enemies shall eat it.

17 ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፥ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ የሚጠሉአችሁም ይገዙአችኋል ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።

17 And I will set my face against you, and ye shall be slain before your enemies: they that hate you shall reign over you; and ye shall flee when none pursueth you.

18 እስከዚህም ድረስ ባትሰሙኝ፥ ስለ ኃጢአታችሁ በቅጣታችሁ ላይ ሰባት እጥፍ እጨምራለሁ።

18 And if ye will not yet for all this hearken unto me, then I will punish you seven times more for your sins.

19 የኃይላችሁንም ትዕቢት እሰብራለሁ ሰማያችሁንም እንደ ብረት፥ ምድራችሁንም እንደ ናስ አደርጋለሁ።

19 And I will break the pride of your power; and I will make your heaven as iron, and your earth as brass:

20 ጕልበታችሁም በከንቱ ያልቃል ምድራችሁም እህልዋን አትሰጥም፥ የምድርም ዛፎች ፍሬአቸውን አይሰጡም።

20 And your strength shall be spent in vain: for your land shall not yield her increase, neither shall the trees of the land yield their fruits.

21 በእንቢተኝነትም ብትሄዱብኝ ባትሰሙኝም፥ እንደ ኃጢአታችሁ መጠን በመቅሠፍት ላይ ሰባት እጥፍ እጨምራለሁ።

21 And if ye walk contrary unto me, and will not hearken unto me; I will bring seven times more plagues upon you according to your sins.

22 በመካከላችሁም የምድርን አራዊት እሰድዳለሁ ልጆቻችሁንም ይነጥቃሉ፥ እንስሶቻችሁንም ያጠፋሉ፥ እናንተንም ያሳንሳሉ መንገዶቻችሁም በረሃ ይሆናሉ።

22 I will also send wild beasts among you, which shall rob you of your children, and destroy your cattle, and make you few in number; and your high ways shall be desolate.

23 እስከዚህም ድረስ ባትቀጡ፥ በእንቢተኝነትም ብትሄዱ፥

23 And if ye will not be reformed by me by these things, but will walk contrary unto me;

24 እኔ ደግሞ በእንቢተኝነት እሄድባችኋለሁ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ።

24 Then will I also walk contrary unto you, and will punish you yet seven times for your sins.

25 የቃል ኪዳኔንም በቀል ይበቀልባችሁ ዘንድ ሰይፍ አመጣባችኋለሁ ወደ ከተማችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ ቸነፈርንም እሰድድባችኋለሁ በጠላትም እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።

25 And I will bring a sword upon you, that shall avenge the quarrel of my covenant: and when ye are gathered together within your cities, I will send the pestilence among you; and ye shall be delivered into the hand of the enemy.

26 የእህላችሁንም ድጋፍ በሰበርሁ ጊዜ፥ አሥር ሴቶች እንጀራቸውን በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፥ በሚዛንም መዝነው እንጀራችሁን ይመልሱላችኋል በበላችሁም ጊዜ አትጠግቡም።

26 And when I have broken the staff of your bread, ten women shall bake your bread in one oven, and they shall deliver you your bread again by weight: and ye shall eat, and not be satisfied.

27 እስከዚህም ድረስ ባትሰሙኝ፥ በእንቢተኝነትም ብትሄዱብኝ፥

27 And if ye will not for all this hearken unto me, but walk contrary unto me;

28 እኔ ደግሞ በቍጣ እሄድባችኋለሁ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ።

28 Then I will walk contrary unto you also in fury; and I, even I, will chastise you seven times for your sins.

29 የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ።

29 And ye shall eat the flesh of your sons, and the flesh of your daughters shall ye eat.

30 የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ የፀሐይ ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።

30 And I will destroy your high places, and cut down your images, and cast your carcases upon the carcases of your idols, and my soul shall abhor you.

31 ከተሞቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፥ መቅደሶቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ መልካሙንም መዓዛችሁን አላሸትትም።

31 And I will make your cities waste, and bring your sanctuaries unto desolation, and I will not smell the savour of your sweet odours.

32 ምድሪቱንም የተፈታች አደርጋለሁ የሚቀመጡባት ጠላቶቻችሁም በእርስዋ የተነሣ ይደነቃሉ።

32 And I will bring the land into desolation: and your enemies which dwell therein shall be astonished at it.

33 እናንተንም ከአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።

33 And I will scatter you among the heathen, and will draw out a sword after you: and your land shall be desolate, and your cities waste.

34 በዚያም በተፈታችበት ዘመን ሁሉ እናንተም በጠላቶቻችሁ ምድር ሳላችሁ፥ ምድሪቱ ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች በዚያም ጊዜ ምድሪቱ ታርፋለች፥ ሰንበትንም በማድረግዋ ትደሰታለች።

34 Then shall the land enjoy her sabbaths, as long as it lieth desolate, and ye be in your enemies’ land; even then shall the land rest, and enjoy her sabbaths.

35 እናንተ ተቀምጣችሁባት በነበረ ጊዜ በሰንበቶቻችሁ አላረፈችም ነበርና በተፈታችበት ዘመን ሁሉ ታርፋለች።

35 As long as it lieth desolate it shall rest; because it did not rest in your sabbaths, when ye dwelt upon it.

36 በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።

36 And upon them that are left alive of you I will send a faintness into their hearts in the lands of their enemies; and the sound of a shaken leaf shall chase them; and they shall flee, as fleeing from a sword; and they shall fall when none pursueth.

37 ማንም ሳያሳድዳቸው ከሰይፍ እንዲሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ እናንተም በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።

37 And they shall fall one upon another, as it were before a sword, when none pursueth: and ye shall have no power to stand before your enemies.

38 በአሕዛብም መካከል ታልቃላችሁ፥ የጠላቶቻችሁም ምድር ትውጣችኋለች።

38 And ye shall perish among the heathen, and the land of your enemies shall eat you up.

39 ከእናንተም ተለይተው የቀሩት በጠላቶቻቸው ምድር ላይ በኃጢአታቸው ይከሳሉ በአባቶቻቸውም ኃጢአት ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይከሳሉ።

39 And they that are left of you shall pine away in their iniquity in your enemies’ lands; and also in the iniquities of their fathers shall they pine away with them.

40 በእኔም ላይ በእንቢተኝነት ስለ ሄዱብኝ የበደሉኝን በደል፥ ኃጢአታቸውንም፥ የአባቶቻቸውንም ኃጢአት ይናዘዛሉ።

40 If they shall confess their iniquity, and the iniquity of their fathers, with their trespass which they trespassed against me, and that also they have walked contrary unto me;

41 እኔም ደግሞ በእንቢተኝነት ሄድሁባቸው ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አገባኋቸው ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የኃጢአታቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥

41 And that I also have walked contrary unto them, and have brought them into the land of their enemies; if then their uncircumcised hearts be humbled, and they then accept of the punishment of their iniquity:

42 እኔ ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ ደግሞ ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ ምድሪቱንም አስባለሁ።

42 Then will I remember my covenant with Jacob, and also my covenant with Isaac, and also my covenant with Abraham will I remember; and I will remember the land.

43 ምድርም ከእነርሱ መጥፋት የተነሣ ባዶ ትቀራለች እነርሱም ሳይኖሩ በተፈታችበት ዘመን ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች ፍርዴንም ስለ ናቁ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የኃጢአታቸውን ቅጣት ይሸከማሉ።

43 The land also shall be left of them, and shall enjoy her sabbaths, while she lieth desolate without them: and they shall accept of the punishment of their iniquity: because, even because they despised my judgments, and because their soul abhorred my statutes.

44 ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝኛ እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም።

44 And yet for all that, when they be in the land of their enemies, I will not cast them away, neither will I abhor them, to destroy them utterly, and to break my covenant with them: for I am the Lord their God.

45 እኔ አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸውን የአባቶቻቸውን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስባለሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

45 But I will for their sakes remember the covenant of their ancestors, whom I brought forth out of the land of Egypt in the sight of the heathen, that I might be their God: I am the Lord.

46 እግዚአብሔርም በእርሱና በእስራኤል ልጆች መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ ያደረጋቸው ሥርዓቶችና ፍርዶች ሕግጋትም እነዚህ ናቸው።

46 These are the statutes and judgments and laws, which the Lord made between him and the children of Israel in mount Sinai by the hand of Moses.