መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #5
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 5 |
Ps 5 |
1 አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ ጩኸቴንም አስተውል |
1 Give ear to my words, O Lord, consider my meditation. |
2 የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና። |
2 Hearken unto the voice of my cry, my King, and my God: for unto thee will I pray. |
3 በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም። |
3 My voice shalt thou hear in the morning, O Lord; in the morning will I direct my prayer unto thee, and will look up. |
4 አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም። |
4 For thou art not a God that hath pleasure in wickedness: neither shall evil dwell with thee. |
5 በከንቱ የሚመኩ በዓይኖችህ ፊት አይኖሩም ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ። |
5 The foolish shall not stand in thy sight: thou hatest all workers of iniquity. |
6 ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል። |
6 Thou shalt destroy them that speak leasing: the Lord will abhor the bloody and deceitful man. |
7 እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ። |
7 But as for me, I will come into thy house in the multitude of thy mercy: and in thy fear will I worship toward thy holy temple. |
8 አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ መንገዴን በፊትህ አቅና። |
8 Lead me, O Lord, in thy righteousness because of mine enemies; make thy way straight before my face. |
9 በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው በምላሳቸው ይሸነግላሉ። |
9 For there is no faithfulness in their mouth; their inward part is very wickedness; their throat is an open sepulchre; they flatter with their tongue. |
10 አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና። |
10 Destroy thou them, O God; let them fall by their own counsels; cast them out in the multitude of their transgressions; for they have rebelled against thee. |
11 በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል ለዘላለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለህ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ። |
11 But let all those that put their trust in thee rejoice: let them ever shout for joy, because thou defendest them: let them also that love thy name be joyful in thee. |
12 አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን። |
12 For thou, Lord, wilt bless the righteous; with favour wilt thou compass him as with a shield. |