መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #9
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 9 |
Proverbs 9 |
1 ጥበብ ቤትዋን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች። |
1 Wisdom hath builded her house, she hath hewn out her seven pillars: |
2 ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን ደባለቀች፥ ማዕድዋን አዘጋጀች። |
2 She hath killed her beasts; she hath mingled her wine; she hath also furnished her table. |
3 ባሪያዎችዋን ልካ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች። |
3 She hath sent forth her maidens: she crieth upon the highest places of the city, |
4 አላዋቂ የሆነ ወደዚህ ፈቀቅ ይበል አእምሮ የጐደላቸውንም እንዲህ አለች። |
4 Whoso is simple, let him turn in hither: as for him that wanteth understanding, she saith to him, |
5 ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ። |
5 Come, eat of my bread, and drink of the wine which I have mingled. |
6 አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ። |
6 Forsake the foolish, and live; and go in the way of understanding. |
7 ፌዘኛን የሚገሥጽ ለራሱ ስድብን ይቀበላል፥ ኅጥአንም የሚዘልፍ ነውርን ያገኛል። |
7 He that reproveth a scorner getteth to himself shame: and he that rebuketh a wicked man getteth himself a blot. |
8 ፌዘኛን አትገሥጽ እንዳይጠላህ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል። |
8 Reprove not a scorner, lest he hate thee: rebuke a wise man, and he will love thee. |
9 ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል። |
9 Give instruction to a wise man, and he will be yet wiser: teach a just man, and he will increase in learning. |
10 የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው። |
10 The fear of the Lord is the beginning of wisdom: and the knowledge of the holy is understanding. |
11 ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃልና። |
11 For by me thy days shall be multiplied, and the years of thy life shall be increased. |
12 ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። |
12 If thou be wise, thou shalt be wise for thyself: but if thou scornest, thou alone shalt bear it. |
13 ሰነፍ ሴት ሁከተኛ ናት አሳብ የላትም፥ አንዳችም አታውቅም። |
13 A foolish woman is clamorous: she is simple, and knoweth nothing. |
14 በቤትዋ ደጅ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ በወንበር ላይ ትቀመጣለች፥ |
14 For she sitteth at the door of her house, on a seat in the high places of the city, |
15 በመንገድ የሚያልፉትን አካሄዳቸውንም ያቀኑትን ለመጥራት። |
15 To call passengers who go right on their ways: |
16 አላዋቂ የሆነ ወደዚህ ፈቀቅ ይበል አእምሮ የጐደለውንም እንዲህ አለች። |
16 Whoso is simple, let him turn in hither: and as for him that wanteth understanding, she saith to him, |
17 የስርቆት ውኃ ይጣፍጣል፥ የተሸሸገም እንጀራ ደስ ያሰኛል። |
17 Stolen waters are sweet, and bread eaten in secret is pleasant. |
18 ነገር ግን እርሱ ሙታን ከዚያ እንዳሉ፥ እድምተኞችዋም በሲኦል ጥልቀት እንዳሉ አያውቅም። |
18 But he knoweth not that the dead are there; and that her guests are in the depths of hell. |